1 |
ፍቅር ፈልገነው አስበነው፣ አባዝተን፣ ቀንሰን አሊያም ደምረን የምናገኘው ቀላል ስሌት አይደም። ፈሪ ሆንክ ደፋር፣ ሀብታም ሆንክ ደሀ፣ ማንም ሆነክ ምንም የማይደንቀው፣ በማንኛውም የሰው ልጅ ልብ ውስጥ በራሱ ጊዜና መንገድ ሰርጎ የሚገባ የተፈጥሮ ፀጋ ነው። ይህን የተሳጠንን ታላቅ ፀጋ (በረከት) መቋደስ መታደል ነው። እስቲ ስለ ፍቅር ካነሳን አይቀር ስለአንድ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ገጠመኝ ላውጋችሁ ልብ ብላችሁት በትእግገስትም አንብቡት፡፡. |
2 |
አንድ በጣሙን ደሃ የሆነ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡ አንድ ቀን ሚስቱ ጸጉሯን የምታበጥርበት ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው፡፡ ባል በጣም አዘነ፡፡ በኪሱ አንዳችም ገንዘብ ስለሌለው እያዘነ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሌላው ይቅርና በቅርቡ ማሰሪያው ለተበጠሰበት የእጅ ሰዓቱ እንኳ ማሰሪያ መግዛት ስላልቻለ በኪሱ ይዞት እንደሚዞር ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት እያሳየ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሚስትም ነገሩን ተወችው፡፡ ባል ወደ ሥራ ሲሄድ በአንድ የሰዓት መሸጫ በኩል ሲያልፍ ወደ መሸጫው ገብቶ ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት ሸጠ፡፡ ሌላ ሱቅ ገባ፡፡ ለሚስቱ በጣም የሚያምር. |
3 |
ማበጠሪያ ገዛ፡፡ ምሽት ላይ ከስራ ወደ ቤት ሲመለስ ዋንኛ ዕቅዱ ለሚስቱ እንዴት ያንን የሚያምር ማበጠሪያ እንደሚሰጣት ነበር፡፡ ሚስቱን ሲያያት ግን ደነገጠ፡፡ ያ የሚያምረው ዘንፋላ ጸጉሯ በአጭሩ ተቆርጧል፡፡ ባለማመን እንደተዋጠ የገዛላትን ማበጠሪያ ከቦርሳው አውጥቶ ወደ እሷ ቀረብ ሲል አይኗ በእንባ እንደረጠበ በእጆቿ መሃል የያዘችውን ነገር ተመለከተ የሰዓት ማሰሪያ፡፡ ሰዓቱን ሸጦ ማበጠሪያ እንደገዛላት ሁሉ፣ ለካንስ እሷም ያን ዘንፋላ ጸጉሯን አስቆርጣ ሸጣ የሰዓት ማሰሪያ ገዝታለት ነበር፡፡ ሁለቱም ፍቅር በልባቸው እየነደደ በእንባ ታጠቡ. |
4 |
ፍቀር ራሱን ንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም አይቀበልም ፍቅር ለፍቅር በቂ ነውና፡፡ ፍቅር ብዙ ነገር ነው ተፅፎ ተነግሮና ተገልፆ የማያበቃ ለከት የሌለው፣ ልንገድበው የማንችል የተፈጥሮ አምባገነን ነው። ፍቅር ውስጣችን ሰርጎ ከገባ ተልካሻ ነገሮች አይምሮአችን ውስጥ ቦታ የላቸውም። ፍቅር ያለ ቦታው የአባጨንጓሬን ያህል ይኮሰኩሳል ቢሆንም በፍቅር አይን. |
5 |
ሁሉም ነገር ትክክል ሰለሆነ በዚህ መኮስኮስ ውስጥም ፍቅር አለ። በፍቅር አለም አለመግባባት አልያም ግጭቶች መፈጠሩ አይቀሬ ነው ምክንያቱም ሰው ሆኖ ፍጹም የለምና ነገር ግን ይቅር ማለት ሁልጊዜ አንተ ተሳስተሃል ማለት አይደለም አንዳንድ ጊዜም ላለህግንኙነት ዋጋ መስጠት ራስ ወዳድነትን መስበር ማለት ነው። ሁላችንም ፍቅርን እንደ ሸማ ለብሰን በፍቅር ኖረን በፍቅር እንድናልፍ እግዚአብሄር ይርዳን።. |
6 |
አባባሎች ከ ጋሽ ስብሃት በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።:" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን. |
7 |
ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።:ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣. |
8 |
ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"አንድ ነገር ልንገራችሁ!:በህይወትሁ ማንንም አትውቀሱጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀልመጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀልክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀልምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል።. |
9 |
መርጦ ለማርያም ማርያም ቤተ-ክርስትያን ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ገዳምበጎጃም ክፍለ ሀገር ከሚገኙት ቅዱሳት አያሌ ገደማት መካከል አንዷ የታላቋ እና የጥንታዊቷ ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ገዳም የምትገኘው ናት ፡፡ ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ገዳም የምትገኘው በጎጃም ክፍለ ሀገር በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ርእሰ ከተማ መርጡለ ማርያም ሲሆን ከአዲስ አበባ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከባሕር ጠለል በላይ በ2,405 ሜትር ከፍታ በቀጥታልኬት በወፍ በረር በ128 ማይል ( 206 ኪ.ሜ ) በመኪና መስመር ደግሞ በደጀን ጒንደ. |
10 |
ወይን መስመር 364 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በላቲቲዩድ 10 49'60" ሰሜን እና በ38 16'0" ሎንግቲዩድ ምስራቅ ድግሪ ሚኑት ሴኮንድ ወይም በ10.8333 እና በ38.2667 ዴሲማል ድግሪ በመርጡለ ማርያም ከተማ ትገኛለች ፡፡መርጡለ ማርያም ትርጉሙ ፦ የማርያም አዳራሽ ማለት ነው ፡፡ ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ገዳም አሁን የያዘችውን የስም መጠሪያ ከመያዟ በፊት በተለያዩ ዘመናት አራት ጊዜ የስም መለዋወጦች አጋጥሟታል ፡፡ መጀመሪያ ሀገረ ሰላም ተብላለች ቀጥሎ ሀገረ እግዚአብሔር ተብላለች. |
11 |
ከዚያም ጽርሐ አርያም ተብላ ተጠርታለች በመጨረሻም አሁን የምትጠራበትን መርጡለ ማርያም የሚለውን ስያሜ አግኝታለች ፡፡የገዳሟ አስተዳዳሪ ርእሰ ርኡሳን የሚል ስያሜ አለው ፡፡ ይች ታላቅ እና ጥንታዊት ገዳም የተመሰረተችው ከእስራኤሉ ንጉሥ ሰሎሞን እና ከኢትዮጵያዊት ንግሥት ሳባ (ማክዳ) የተወለደው ቀዳማዊ ምኒሊክ ይዟቸው በመጣ ፫፻፲፰ የኦሪት ካህናት በአራት ሺ አምስት መቶ ዓመተ ዓለም ነው ፡፡ ወደ ዚች ቦታ የመጡት የኦሪት ካህናት መሥዋተ ኦሪትን በመሰዋት የኦሪትን. |
12 |
አምልኮት ሲፈጽሙ ኖረዋል ፡፡ በ፫፻፴፫ ዓ.ም ህሩያን ነገሥታት አብርሃ ወ አጽብሃ ከከሳቴ ብርሃን አባ ሰላማ ጋር በመሆን በዚች ቦታ መጥተው ሕገ ወንጌልን አስተምረዋል ሕዝቡን አጥምቀው ካህናትንሹመዋል ፡፡አምስቱ ተራሮችገድለ አብርሃ ወ አጽብሃ እና ገድለ አባ ሰላማ ከሳቴብርሃን እንደሚያስረዱት ሕሩያን ነገሥታት አብርሃ ወ አጽብሃ ከጳጳሱ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጋር በመሆን በ፫፻፴፫ ዓ.ም አባይን ተሻግረው ጎጃም ምድር መርጡለ ማርያም ደረሱ ፡፡ “ ወአደው ፈለገ. |
13 |
ግዮን አብርሃ ወ አጽብሃ ዘምስለ ሰላማከሳቴ ብርሃን ወበጽሑ ምድረ ጎጃም ” በዚህ ቦታ ሕዝበ ክርስቲያኑን ወንጌል አስተምረው መክረው ከኦሪት ወደ ሐዲስ ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተእግዚአብሔር መልሰው ካጠመቁበኋላሕዝበ ክርስቲያኑ አምልኮቱን የሚፈፅምበት ቤተ ክርስቲያንን ለመስራት አሰቡ ፡፡ ቦታውላይ በጣም የሚያምር ቤተ ምኲራብ ስለ ነበር ይህንን ለታሪክ ትተን ሌላ ቦታ ላይ እንስራ በማለት በስተ ምሥራቅ አሻጋሪ ካለው ተራራ አሁን ግንብ ወሬ እየተባለ. |
14 |
ከሚጠራው ኮረብታ ለይ ቁፋሮ ጀመሩ ፡፡ ነገር ግን መሬቱ የእሳት ትንታግ እየተፋ አልቆፈር አለ ፡፡ በመሆኑም በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን እንሰራ ዘንድ እግዚአብሔር አልፈቀደም ፈቃደ እግዚአብሔርን እናውቅ ዘንድ ለ፫ ተከታታይ ቀናት ሱባኤ እንግባ በማለት በ፭ በአካባቢው ባሉ የተለያዩ ኮረብታዎች ሱባኤ ገቡ ፡፡ሱባኤየገቡባቸው ከረብታዎች የሚከተሉት ናቸውየኦሪቱ ሊቀ ካህንአብኒ ከተባለው ኮረብታየሐዲሱ ሹም ሐዲስጌ ከተባለው ኮረብታጳጳሱ አቡነ ሰላማ ሰላምጌ ከተባለው. |
15 |
ኮረብታንጉሥ አብርሃ አብርሂ ከተባለው ኮረብታንጉሥ አጽብሃ ዜነዎ ከተባለው ኮረብታንጉሥ አጽብሃም ከሁሉም አስቀድሞ ወደ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንበመሄድ ያየውን ራዕይ ተናገረ ፡፡ ሌሎችም መጥተው ያዩትን ሁሉ ተናገሩ አባ ሰላማም ይህንን ራዕይ ያዩ መሆናቸውን ነገሯቸው፡፡ሁሉም በአንዲት ሌሊት አንድ ዓይነት ራዕይ አዩ ፡፡ ያዩት ራዕይም ፦ “ ዐሥራሁለት በሮች ያላትአንድ አምደ ብርሃንየቤተ መቅደሱ መሰረትከተጀመረበት ኮረብታ ተነስታእያበራች የጥንቱ ቤተምኲራብ. |
16 |
ከሚገኝበትጽርሐ አርያም አምባላይ ስታርፍ ” ነበር ፡፡ጧት ወደ ቦታውሲሄዱ የጥንቱ አስደናቂውቤተ ምኲራብ መሬትውስጥ ተቀብሮ ለጥያለ አረንጓዴ ሜዳሆኖ አገኙት ፡፡“ ወእም ድህረዝ ፈቀዱ አብርሃ ወ አጽብሃከመ ይህንጽ መቅደስ በህየ ወሐነጹ ማህደረ ሰናይተ ወገብሩ አረፋቲሃ ዘወርቅ ወዘብሩር ወሴሙ ካህናተ ወዲያቆናተ ወአስተሳነዩ ኲሎሥርዓተ ወሴሙ በውስቴታ ርእሰ ርኡሳን ዘውእቱ ሊቀ ካህናት ወሰመይዋ ለይእቲ መቅደስ መርጡለ ማርያም ” ነገሥታቱ አብርሃ ወ አጽብሃበቦታው ቤተ. |
17 |
መቅደስን ይሰሩ ዘንድ ወደዱ በወርቅ እና በእንቍ አምዶችን እና አረፍቶችን ልዩ አድርገው በማስጌጥ የማርያምን ቤተመቅደስ ሰሩ ፡፡ ሥርዓትንም በመደንገግ ካህናትን ዲያቆናትን እንዲሁም ሁሉንም ሊያስተዳድር የሚችል ሊቀ ካህናት ርእሰ ርኡሳን ብለውሾሙ ፡፡ መቅደሷንም መርጡለ ማርያም ብለው ሰየሟት ፡፡ ንጉሥ አብርሃወ አጽብሃም እግዚአብሔርበመራቸው መሰረት በጳጳሱበአባ ሰላማ አስባርከውበጽርሐ አርያም አምባላይ አስደናቂውንባለ ፲፪ ቤተመቅደስ ባለ ፩ ፎቅቤተ መቅደስ. |
18 |
ሰርተውበወርቅ በእንቊ በከበሩማዕድናት አስጊጠው ጥር፳፩ ቀን የእመቤታችንንጽላት አስገብተውቅዳሴ ቤቱን አከበሩ፡፡ ንጉሥ አብርሃ ወ አጽብሃ ቤተ መቅደስለመስራት መጀመሪያ ቁፋሮየጀመሩበት ተራራ አሁንም ግንበ ወሬ እየተባለ ይጠራል በወሬ የቀረ ግንብ ማለት ነው ፡፡ በዚህ የተነሳ ንጉሥ አጽብሃ በመጀመሪያመጥቶ ራዕዩን ስለ ተናገረ ሱባኤ የገባበት ኮረብታ ዜነዎ ሲባል ሌሎች አባቶች ሱባኤ የያዙባቸው ኮረብታዎች አሁንም በየስሞቻቸውእየተጠሩ ሕያው የታሪክ. |
19 |
ምስክሮች ሆነው ይገኛሉ ፡አብርሃ ወ አጽብሃ በዚች ቦታ ላይ በ፫፻፴፫ ዓ.ም ባለ ፲፪ ቤተ መቅደስ እና ባለ ፩ ፎቅ ቤተ ክርስቲያን አንጸው የእመቤታችንን ጽላት ጥር ፳፩ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስገበተዋል ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን እጅግ የተለየ በልዩ ልዩ ቅርፅ ያጌጠ በወርቅ እና በእንቁ የተለበጠ አስደናቂ የጥበብ አሻራ ያረፈበት ነበር ፡፡ ይህ ቤተ መቅደስ በዮዲት ጉዲት ዘመን በ፰፻፵፪ዓ.ም ተቃጥሏል ፡፡ ከቃጠሎው የተረፈው ፍርስራሽ አሁንም አለ ፡፡ በ፰፻፹፪ ዓ.ም የነገሰው. |
20 |
አንበሳ ውድም በዮዲት የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን እንደገና አሰርቶታል ፡፡ ነገር ግን አብርሃ ወ አጽብሃ ያሰሩት ባለ ፲፪ ቤተ መቅደስ እና ባለ ፩ ፎቅ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለመስራት በጣም አስቸጋሪ ሰፊ ታላላቅ ሙያተኞችን የሚጠይቅ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ውስብስብ እና ጥልቅ ጥበብ የሚጠይቅ በመሆኑ መልሶ ለመስራት አልቻለም ፡፡ በመሆኑም ከተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ሌላ የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን አሰርቷል ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን አሁንምበአገልግሎት ላይ አለ ፡፡. |
21 |
ይህንን ቤተ ክርስቲያንን ከነሐሴ ፳፮ ፲፬፻፷ ዓ.ም - ኅዳር ፲ ፲፬፻፸ ዓ.ም የነገሠው ንጉሥ ዐፄ በእደ ማርያም በ፲፬፻፷ ዓ.ም አሳድሶታል ፡፡ ባለቤቱ ንግሥት እሌኒ ደግሞ የአንባውን ዙሪያ አሰርታለች አሁንም የገዳሟ ዙሪያ የእሌኒ ውድሞ ይባላል ፡፡ ንጉሠ ነገሠት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም ሌላ ቤተ ክርስቲያን በዚች ገዳም ውስጥ አሰርተዋል ፡፡ የቅድስት ሥላሴ እና የቅዱስ ገብርኤል ጽላት ይገኝበታል ፡፡ እንደገናም በ፲፱፻፸፫ ዓ.ም በወቅቱ የገዳሟ አስተዳዳሪ. |
22 |
የነበሩት ርእሰ ርኡሳን አባ ለእከ ማርያም ከሳር ክዳን አሁን ወዳለበት ቆርቆሮ ክዳን አሳደሰውታል ፡፡ በዚች ገዳም ውስጥ ፫ ቤተ ክርስቲያን አሉ ፡፡ ፩. አብርሃ ወ አጽብሃ ያሰሩት የእመቤታችን ቤተ መቅደስ ፪. ነጉሥ አንበሳ ውድም ያሰራው የእመቤታችን ቤተ መቅደስ ፫. ንጉሥ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ያሰሩት የቅድስት ሥላሴ እና የቅዱስ ገብርኤል ቤተ መቅደስ ናቸው ፡፡. |
23 |
የሚገርም የፍቅር ታሪክ ፍቅረኛሞቹ አንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ነው የሚማሩት፡፡ ብዙ ጊዜተለያይተው አያውቁም፡፡ አንድ ቀን ግን ያለልማዳቸው ተለያዩ፡፡ሴትዋ ወደ ዩኒቨርስቲው ሳትመጣ ቀረች፡፡ "ፍቅረኛዋ ምን ሆናይሆን የቀረችው?" እያለ በሐሳብ እየተጨነቀ እያለ ስልኩተደወለ፡-እሱ፡ ሃይ የኔ ማርእሷ፡ ሃይ እንዴት ነህእሱ፡ ውዴ ዛሬ ወደ ግቢ አልመጣሽም በሰላም ነው? በጣምናፍቀሽኛል!እሷ፡ በሰላም ነው የኔ. |
24 |
ቆንጆ፡፡ ትንሽ አሞኝ ሐኪም ቤት ሄጄነበር፡፡እሱ፡ ምንድን ነው! ምን ነካብኝ የኔ ንግሥት?እሷ፡ አይ ምንም ከወቅቱ የአየር ሁኔታ ጋር የተያየዘ ነው፡፡ አሁንደህና ነኝ ተሽሎኛል፡፡እሱ፡ አሁን የት ነው ያለሽው እመጣለሁ?እሷ፡ ኖኖ ችግር የለውም አትምጣ፡፡ አባዬ ከኔ ጋር ስላለአይመችም፡፡ ግን እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?እሱ፡ እሺ ጠይቂኝእሷ፡ ምን ያህል ታፈቅረኛለህ?እሱ፡ የዛሬ ደግሞ ምን ዓይነት ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ካለውሁሉ አብልጬ አፈቅርሻለሁ፡፡ ሕይወቴ ዓለሜ አንቺ ነሽ. |
25 |
ሌላሕይወት ሆነ ዓለም የለኝም፡፡እሷ፡ ዋው አመሰግናለሁ!እሱ፡ ግን ለምን ጠየቅሽኝ?እሷ፡ ዝምታእሱ፡ ችግር አለ? በጥልቅ ስሜት እንደማፈቅርሽ እያወቅሽለምንጠየቅሽኝ?እሷ፡ አረ ምንም ምን ያህል እንደምታፈቅረኝ ለማወቅ ያህልነው፡፡ ግን እኔን ታስብልኛለህ?እሱ፡ በጣም! በዚህ ዓለም ያለችኝ እስትንፋሽ ላንቺ ነውየማበረክታት፡፡ እኔ ሞቼ አንቺ እንድትኖሪ ነው የሁልጊዜ ምኞቴናሕልሜ፡፡እሷ፡ እርግጠኛ ነህ እስትንፋሽህ ለኔ ትሰጠኛለህ?እሱ፡ ምንም አትጠራጠሪ! ግን ችግር አለ? ምንድን. |
26 |
ነውያለአመልሽ መጠራጠር አበዛሽ?እሷ፡ አረ ምንም ያጋጠመ ችግር የለም፡፡ ሁሉም ነገር ሰላምነው የኔ ጌታ፡፡እሱ፡ እኔ እንጃ እስቲ ይሁን፡፡ እኔ ግን ምን እንደሆነ እንጃ ፍርሃትፍርሃት ይለኛል፡፡እሷ፡ ምንም አትፍራ ግን ለእርሷ ብለህ ሙት ብትባል ለእኔብለህ ትሞታለህ?እሱ፡ አዎ ላንቺ ብዬ ራሴን አጠፋለሁ፡፡ ላንቺ ብዬ ገመድአንገቴላይ አስገብቼ ራሴን ቂቅ አድርጌ እገድላለሁ፡፡እሷ፡ ዋው ሪሊ!እሱ፡ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንቺ ልጅ ግን ለምንድን ነውእነዚህ ጥያቄዎች የምትጠይቂኝ?. |
27 |
በሰላም ነው?እሷ፡ ኖ ሁሉም ነገር ሰላም ነው ዝም ብዬ ለማረጋገጥ ያህልነው፡፡ አየህ ስለቀጣዩ ሕይወታችን ለማሰብ ስላንተ እርግጠኛመሆን አለብኝ፡፡እሱ፡ ኦኬእሷ፡ አባዬ እየጠራኝ ነው ባይ የኔ ቆንጆእሷ፡ ቻው ከልብ አፈቅርሻለሁ፡፡በሚቀጥለው ቀን ካምፓስ ውስጥ እሱ ከወንድ ጓደኛው ጋርተገናኙ፡፡እሱ፡ ሃይ ፍቅረኛየ አይታሃታል እንዴ? ዛሬም አልመጣችምመሰለኝ?ጓደኛ፡ ባለጉዳይ. |
28 |
ያላየሃት እንዴት እኔ አያታለሁ?እሱ፡ ባክህ ትናንት ምን እንደሆነች በመዓት ጥያቄዎችስታጣድፈኝ ነው ያመሸችው፡፡ጓደኛ፡ አንተ ጅል እሷ ዝም ብላ ነው ለጊዜ ማሳለፊያየምትጠቀምብህእሱ፡ አፍህ ብትይዝ ይሻላል አንተ ሰውዬ የሷ ክፉ ነገርእንድትናገረኝ አልፈልግም፡፡ጓደኛ፡ ወዳጄ ከዚህ ውጭ ምንም ልልህ አልችልም፡፡የዕለቱ የትምህርት ክፍለጊዜ አልቆ ወደ ዶርማቸው ሄዱ፡፡ፍቅረኛውን ደወለላት፡፡እሷ፡ ሃይ እንዴት ነህልኝ?እሱ፡ ደህና ነኝ ተሽሎኛል አላልሽም እንዴ? ዛሬስ ለምን. |
29 |
ቀረሽ?እሷ፡ የዶክተር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡እሱ፡ አሁን ገባኝ በእኔ ላይ እየቀለድሽ እንደሆነ፡፡ ቀጠሮሽአያልቅ!እሷ፡ እናቴ በቤት ስልክ እደወለች ነው ቻው እሷን ላናግር ነውእሱ፡ ችግር የለም ጨርሺ እጠብቅሻለሁእሷ፡ ኖኖ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ነገ እደውልላሃለሁእሱ፡ በፍፁም ከዚች ንቅንቅ አልልም እያልኩሽልጂቱ ከእናቷ ጋር ይሁን ከሌላ ሰው ጋር የነበራትን ወሬ ጨርሳወደ ፍቅረኛዋ. |
30 |
ተመለሰች፡፡እሷ፡ ለደቂቃዎች በዝምታ ተውጣ ከቆየች በኋላ……..ስማ የኔውድ ስሜትህ በመጉዳቴ ይቅርታ አድርግልኝ ከዛሬ ጀምሮግንኙነታችን እዚህ ላይ እንዲቋጭ ወስኛለሁ፡፡እሱ፡ ምን!እሷ፡ አዎ ለሁለታችን የሚያዋጣው ግንኙነታችን እዚህ ላይእንዲቋጭ ማድረግ ነው፡፡እሱ፡ ለምን ግን ምን በደልኩሽ?እሷ፡ ምንም የበደልከኝ የለህም በጣም እወድሃለሁ ቻውእሱ፡ አንቺ አስመሳይ ችግር. |
31 |
የለውም የኔ ግፍ ይሰጥሻል ቻውመልካም ሕይወትፍቅረኛው ወደ ዩኒቨረስቲው ከመጣች ሦስት ሳምንታት አለፉ፡፡ፍቅረኛዋ ተጣላልቶት ወደነበረው ጓደኛው ጋር በመሄድ ይቅርታጠየቀው፡፡እሱ፡ ጓደኛዬ ይቅርታ አድርግልኝ ለእኔ እንደምታስብልኝ አሁንነው የገባኝ፡፡ጓደኛው፡ ምንድን ነው? ምን ተፈጠረ?እሱ፡ ፍቅረኛዬ ግንኙነታችን እንደተቋረጠ ነገረችኝጓደኛው፡ እኔኮ ይሄ እንዳይፈጠር ነው. |
32 |
ሙሉ በሙሉ ልብህከፍተህ አትስጣት ያልኩህ፡፡ ወይኔ ቁማር ተበላህ፡፡ አይዞህ ሴትብትሄድ ሴት ትመጣለች፡፡ እዚህ ካምፓስ ያሉ የሚያማምሩሴቶች ያንተው ናቸው፡፡እሱ፡ በምንም ተአምር ከአሁን በኋላ ሴት የምትባለውአጭበርባሪ ፍጥረት አላይም፡፡ጓደኛው፡ የእሷ ጓደኛ ታውቃታለህ አይደለ እቺ ማህሌትየምትባለው ይሄ ስልክ ስጠው ብላ ሰጥታኛለች፡፡ ከክላስ በኋላበዚህ ስልክ ደውለን ልክ ልክዋን እንነግራታለን፡፡ክላስ አልቆ ጓደኛሞቹ በግ ተራ ቁጭ ብለው ወደተሳጣቸውስልክ ደወሉ፡፡. |
33 |
ነርስ፡ ሄሎ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ማን ልበል?እሱ፡ በድንጋጤ ትንፋሽ እያጠረው…..በዚህ ስልክ ደውሉተብለን ነበር?ነርስ፡ የሄርሜላ ፍቅረኛ ነህ?እሱ፡ አዎነርስ፡ ፍቅረኛህ ታማ ሆስፒታል ውስጥ ተኝታ ነው ያለችው፡፡ከቻልክ መጥተህ እንድታያት ትፈልጋለች፡፡ ክፍል ቁጥር 320ነው የተኛችው፡፡ አሁን ስራ ስለያዝኩ ብዙ ላወራህ አልችልምቻው!ከዚያ በኋላ እሱና ጓደኛው ኮንትራት ታክሲ ይዘው. |
34 |
ወደ ሆስፒታሉሄዱ፡፡ እውነትም ፍቅረኛው በሞትና በሕይወት መካከል ሆናአገኛት፡፡እሱ፡ ምነው ማሬ ደህና አይደለሽም እንዴ?እሷ፡ ቃላት ማውጣት አቃታት፡፡ ፍቅረኛው በእንዲህ ዓይነትሁኔታ ስላገኛት በሐዘን ኩምትር ብሎ አምርሮ አለቀሰ፡፡ በዚህመሃል የፃፈቸው ማስታወሻ እንዲያነበው በእጇ አመላከትችው፡፡ወረቁቱን አንስቶ ማንበብ ጀመረ፡-"ወዴ ዛሬ የጠራሁህ ልሳነበትህ ነው፡፡ ካንተ ጋር. |
35 |
ብኖር ደስታዬአልችለውም ነበር ግን አልቻልኩም፡፡ ካንሰር የተባለው ሕመምይዞኝ በመጨረሻዋ የሕይወቴ ምዕራፍ እገኛለሁ፡፡ ግንኙነታችንቀደም ብሎ እንዲቋረጥ የፈለግኩት የኔ ዘላለማዊ መለየትድንገት እንዳይሆንብህ፣ እየተለማመድክ እንድትቆይ ብዬ ነው፡፡ቻው እስከዘላለሙ አፈቅራሃለሁ" ይል ነበር፡፡ፍቅረኛዋ እጅዋን ይዞ ደም አነባ፡፡ በደምብ አልቅሶ ሳይወጣለትነርሷ መጥታ ከክፍሉ እንዲወጣ አዘዘችው፡፡ በነጋታው ወደሆስፒታሉ ሲሄድ ፍቅረኛው አርፋለች፡፡. |
36 |
የሚወዳትን ፍቅረኛውንከቀበረ በኋላ እርሱም በተራው በሻወር ቤቱ ውስጥ ራሱንአጥፍቶ ተገኘ፡፡ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት የፃፈው ማስታወሻሲነበብ እንዲህ ይል ነበር፡"ውዴ ታስታውሺ ከሆነ ያላንቺ እንደማልኖር ገልጬልሽ ነበር፡፡አዎ አንቺ ለእኔ ብለሽ እንደሞትሽ ሁሉ እኔም ላንቺ ብየ ለመሞትወስኛለሁ፡፡ ቃልሽን ጠብቄም ተከትየሻለሁ!". |
Комментарии